ሀገሬ አንዳንዴ ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የዘረጋሻቸውን ጎዳናዎች፣ ልታነጥፊያቸው ደፋ ቀና የምትይላቸውን ሀዲዶች ስመለከት ደስ ይለኛል። የአዲስ አበባን አስፋልትና በየአስፋልቱ ዳር ያቆምሻቸውን ህንፃዎች አዲስነት ስመለከት ደግሞ፣ ‹‹ቆይ ሀገሬ፣ መንገድም፣ ህንፃም አልነበራትም እንዴ?›› ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ሀገሬ ግንባታሽን ለተመለከተ ፈርሶ የሚሰራ ሀገር ነው እኮ የምትመስይው! ግን እኔ ልማትሽን፣ እድገትሽን፣ ትራንስፎርሜሽንሽን . [...]
↧