የኢትዮጵያ ልዩ መጠሪያዎች ከሚባሉት መካከል “ሰው አክባሪነት” አንዱ ነው፡፡ በበርካታው የአገራችን ባህል ሰዎች በዕድሜያቸው የአንቱነትን ማዕረግ ይጎናጸፋሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በሥራቸው፣ በሙያቸው፣ በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ከበሬታ ይህ የአንቱነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በዕድሜያቸው በጣም ልጆች የሆኑ እንኳን ባላቸው መንፈሣዊ አገልግሎት ወይም ልዕልና በታላላቆቻቸው ሳይቀር አንቱ ይባላሉ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን አንቱ ብሎ መጥራት ለኢትዮጵያዊ የሚነገረው ወይም የሚማረው ግብረገብ አይደለም፡፡ እንደ […]
↧