አጉል ዘመን ገጥሟት በረት ብትከሳ፤ ከብቶች በመዥገሮች አዩ ብዙ አበሳ፡፡ ጡቶቿን አቃጣይ የነበልባል ጥጃ ላም እሳት ወለደች፤ ብ’ተው በማይተዋ ዘልለው ባልጠገቡ ወይፈኖች ነደደች፡፡ የከበረው ባህል ባለጌ ረጋግጦት እንደጨው ቀለለ፤ ወፍ ዘራሾች ነግሠው ባጥለቀለቁት ደም ምድር ተበከለ፡፡ አዎ፣ ላም እሳት ወለደች! እንደዮዲት ጉዲት እቶኑ የሚፋጅ፤ ዕረፍት በማያ’ቅ ሠይፍ እንደነደርቡሾች እንደግራኝ አህመድ፤ ጭንቅላትን ገምሶ አንገትን ቆራርጦ ዜጎችን […]
↧