ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ። መስታወታቸው ረግፏል፤ ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም። የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል። የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል። ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ […]
↧