የማኅበራዊ ሚዲያ ሰለባዎች ዓይነታቸው ብዙ ነው። ልጆቻቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተግዳሮቶችን (ቻሌንጅ) በመውሰድ እልህ ውስጥ ገብተው የሞቱባቸው ጥቂቶች አይደሉም። “Blackout Challenge” የተሰኘው የቲክቶክ ተግዳሮት ፉክክር ውስጥ የገቡ ሕጻናትና ወጣቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሌሎች ጥቂት የማይባሉ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያ ሱሰኛ ሆነው ሕይወታቸው የተበላሸ አሉ። የተጎጂው ቁጥር ሥፍር የለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮቹን የሚከስሱ ወላጆች ቁጥርም እንዲሁ እጅግ በርካታዎች ናቸው። […]
↧