Quantcast
Channel: Goolgule
Browsing all 518 articles
Browse latest View live

ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”

እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ...

View Article


የታሪክ ፈተናችን እና ያሬዳዊ ትዝታ፤ ከክላሽ እስከ ብዕር!

የለውጥ ውርጃ፣ የዘመናዊነት መጨናገፍ፣ የህዝባዊ ኃይል (ድምጽ) ተጽኖ ፈጣሪነት መኮላሸት፣…ድግግሞሻዊ የታሪክ አዙሪት አምሳያ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በተከታታይ ትውልዶች የደም ጎርፍ እየተንሳፈፈች እዚህ ደርሳለች። የአገር ግንባታ ሲሚንቶ ውሉ አልይዝ ብሎ ንቃቃት በዝቶበት የታሪክ ፈተናዋን መሻገር የተሳናት ኢትዮጵያ፤...

View Article


የሱሪ ረዥሙ “ፕሮፌሰር ጄኔራል” ሳሞራ የኑስ ስንብትና የሳዕረ መኮንን መንገሥ

ግንቦት 30/2010 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ማምሻውን ከወደ ታችኛው ቤተ-መንግሥት የተሰማው ዜና የኢትዮጵያዊያንና የዓለምአቀፉን ሚዲያ ትኩረት የሳበ ነበር። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (መከላከያ በአዲሱ አወቃቀር በኮሚቴ (ወታደራዊ ካዉንስል) ሊመራ ነው) በሚል ርዕስ ከሦስት ሳምንት በፊት መከላከያ ሠራዊት እንደተቋም...

View Article

“ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት

ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ...

View Article

የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!

የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሒልተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው...

View Article


“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን

በባድመ ጉዳይ የሰሞኑ የህወሓትና የደጋፊዎቹ የማደናገሪያ ጉንጭ አልፋ ሙግት ብዙዎችን ያሰገረመ ከመሆኑ አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን በፓርላማ በሚያስጠይቅ መልኩ የቀረበ ትዕይንት ሆኖ አልፏል። ራሱ ህወሓት በቆሰቆሰው እሣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በ“ድንበር ተደፈረ” ማጭበርበሪያ ካስማገደ እና የፈንጂ ማምከኛ...

View Article

የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ

ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን...

View Article

የኢትዮ –ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ

ለረዥም ዓመታት በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የዘለቀው ግንኙነት ወጥ የሆነ መልክ ያለው አልነበረም። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከመጽናቱ ቀደም ብሎ በነበሩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በኢትዮ – ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ከግብጽ ተስፋፊ ኃይልና ከሱዳን የንቅናቄ (መሃዲስት) ኃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት...

View Article


የአብዲ ኢሌይ መጨረሻ ሲጀምር

የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ድርጅት (ሒውማን ራይትስ ዎች) በዛሬው ዕለት (ጁላይ 4) “እንደ ሞቱ ሰዎች ነን፤ የሶማሊ ክልል በሚገኘው የዖጋዴን እስር ቤት የሚካሄደው ስቅየትና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች” “We are Like the Dead’: Torture and other Human Rights Abuses in Jail...

View Article


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 100 ቀናት የሥልጣን ጊዜ አስመልክቶ ጽህፈት ቤታቸው በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑትን ጉዳዮች በሚከተለው መልኩ ማብራሪያ ሰጥቶበታል። ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት...

View Article

ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

አፍቃሪ ህወሓት የሚዲያ ተቋማት የማኅበራዊ ድረገጽ ተዋናዮቹን ጨምሮ “ቀለበት ውስጥ ገብተናል” በማለት የተጀመረውን ለውጥና ከኤርትራ ጋር የተያዘውን አስደማሚ የሰላም ሂደት ሲቃወሙ ሰንበተዋል። አሁንም ምክንያት በመለጣጠፍ እየተቃወሙ ነው። ድርጅታቸው ህወሓት የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን...

View Article

የህወሃትና ኦብነግ የትግል አጋርነት –በንጹሃን ደም ሲታተም አየን!!

በሚያዚያ 1999 አቦሌ በሚባለው የነዳጅ ጉደጓድ መቆፈሪያ ካምፕ 200 የሚጠጉ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ታጣቂዎች በድንገት የፈጸሙት ጥቃት አስደንጋጭና አረመኔነት የተሞላበት ነበር። በወቅቱ ዘጠኝ ቻይናዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰባ አራት ንጹሃን ህይወት አለፈ። በወቅቱ ጥቃቱ የተፈጸመው በሌሊት ሁሉም በተኙበት ሲሆን...

View Article

“የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?

1. የአሜሪካ ሃያልነት ከጃፓን እስከ ቻይና ላለፉት አንድ መቶ አመታት አሜሪካ የዓለም ልዕለ-ሃያል ሀገር መሆኗ እርግጥ ነው። የአሜሪካ ሃያልነት ግን ያለ ተቀናቃኝ በብቸኝነት የዘለቀ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በየግዜው ከሚመጡ ተቀናቃኝ ሀገራትና ቡድኖች ጋር ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ስለዚህ...

View Article


መለስ በቆፈረው ጉድጓድ ሲዘከር

ይህ ቃለ ምልልስ “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ May 20, 2013 አትመነው ነበር። የኢትዮጵያን የውድቀት ጉድጓድ ሲቆፍሩ የነበሩትና በአገዛዝ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ጉድጓዱን በጥልቀት ሲቆፍሩ የነበሩት መለስ ከኢትዮጵያ ቀድመው ጥልቁ ጉድጓድ ገብተዋል። ዛሬ በሙት መንፈስ የሚመሩት “ተዝካራቸውን”...

View Article

“የቻይና ጅብ” ክፍል ፪፡ በብድር ያነክሳል! በዕዳ ጫና ይነክሳል! በወታደር ይጨርሳል!

ቻይናዎች “አንድ ሀገር መበልፀግ ከፈለገ መንገድ መገንባት አለበት” የሚል አባባል አላቸው። በዚህ መሰረት ሀገሪቱ በየብስና ባህር ላይ “የሀር መንገድ” (Silk Road & Silk Maritime) ለመገንባት አንድ (1) ትሪሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። ይህ የሀር መስመር በሚያልፍባቸው 68 ሀገራት ውስጥ 900...

View Article


ኢትዮጵያዊነትና የብሔር ማንነት ተደጋጋፊ ወይስ ተገዳዳሪ?

“ኢትዮጵያ አገራችን የየራሳችን አኩሪ ባህል ያለን፣ የየራሳችን መልክዓ ምድር፣ አሰፋፈር የነበረንና ያለን፣ ብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት አገር በመሆንዋ ያፈራነው የጋራ ጥቅምና አመለካከት አለን ብለን ስለምናምን፣ መጪው የጋራ ዕድላችን...

View Article

መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!

በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ...

View Article


የኢህአዴግ የመጨረሻ ጉባኤ…

ኢህአዴግ መሽቶበታል። አቅሙ ክዶታል። ባልሞት ባይ ተጋዳይነት አለሁ ቢልም ዘላለማዊ ዕንቅልፉ ግን የሚቀርለት አይመስልም። የሜክሲኮውን ፒ አር አይ ፓርቲ አርአያው አድርጎ ሰባ አመታትን እጓዛለሁ ብሎ የተነሳው ድርጅት ግማሽ መንገድ እንኳን ሳይጓዝ ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል። ገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው የርዕዮተዓለም ልዩነት...

View Article

ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ

በደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመንና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል...

View Article

“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች

ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንግናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው...

View Article
Browsing all 518 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>