የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ ድረገጽ መረጃ እንደሚለው ከሆነ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገራት መካከል የአሜሪካንን ዕርዳታ በመቀበል ቀዳሚነቱን ሥፍራ የያዘችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ (http://www.foreignassistance.gov/) የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ወይም በጀት ከተደረገው ውጪ የሚሰጠውን ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማ ሳይጨምር ከ2009 – እስከ 2012 ባሉት ዓመታት ብቻ ኢትዮጵያ ከ3.3ቢሊዮን ዶላር በላይ (በወቅቱ ምንዛሪ ከ60ቢሊዮን ብር በላይ) ዕርዳታ ተቀብላለች፡፡ ገንዘቡ የሚሠጠው ሰላምና ደኅንነት [...]
↧